Learn English in Amharic
Welcome to Tmhrt.com
እዚህ ድህረገጽ ላይ በዋናነት ቀጥለው የተዘረዘሩትን 4 የእንግሊዘኛ ኮርሶች ይማራሉ፦
ይሄን ኮርስ ወስደው ሲጨርሱ፦
- የእንግሊዝኛ ፅሁፍ ማንበብና መፃፍ ይችላሉ።
- መሰረታዊ የእንግሊዘኛ ግራመር ህጎችን ያውቃሉ።
- በማንኛውም አጋጣሚ ሀሳብዎን ለመግለጽ የሚያስችልዎትን እንግሊዘኛ ያውቃሉ።
እነዚህን ውጤቶች ለማምጣት ከእርስዎ የሚጠበቀው ነገር ምንድን ነው? ከእርስዎ አንድ ወሳኝ ነገር ይጠበቃል። እርሱም ለትምህርቱ ከፍተኛ ተነሳሽነትና ትምህርቱ የሚጠይቀውን ነገር መስራት ነው። ለምሳሌ፣ ስንፍናን እና ተስፋ መቁረጥን አስወግዶ ማንበብን፣ የፈተና ጥያቄዎችን መስራትን እና የሚሰጡትን የቤት ስራዎች ባግባቡ መስራትን ይጠይቃል። ይሄን ካደረጉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ያመጣሉ።
ስለዚህ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ምን ያህል አንገብጋቢ እንደሆነብዎት ይገንዘቡ፣ ከዚያም በርትተው፣ ያንብቡ፣ የተማሩትን ምን ያህል እንደተገነዘቡት ለማወቅ የፈተና ጥያቄዎችን ይውሰዱ፣ እንዲለማመዱ የተጠየቁትንም ነገር ይለማመዱ።
እዚህ ድህረገፅ ላይ እንግሊዘኛ ቋንቋን ከአልፋቤት ጀምረው በቀላልይ ይማራሉ። ኮርሶቹ በአማርኛ እየተዘጋጁ የሚቀርቡ ስለሆነ ለመረዳት ቀላል ናቸው። ሁሉም ኮርሶች መጨረሻ ላይ ቀላል የፈተና ጥያቄዎችን ይዘዋል። ክፍያውን ከፍለው ከተመዘገቡ በኋላ የእንግሊዘኛ ትምህርትዎን ለመጀመር ቀጥለው የቀረቡትን ሊንኮች መጠቀም ይችላሉ።
