Back to: ኮርስ 2፦ Parts of Speech (የንግግር ክፍሎች-የእንግሊዘኛ ግራመር ትምህርት)
የእንግሊዝኛ ግራመር አጠናን ቅደምተከተል
መሰረታዊ ግራመር ሲያጠኑ ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ እነዚህን 7 ቅደም ተከተሎች ተከትለው ያጥኑ።
ቀጥለው የቀረቡትን የግራመር ህጎች በትክክል ሲማሩ እንግሊዝኛን በደንብ ይገነዘባሉ።
Step 1: Understand the Basic Parts of Speech (በመጀመሪያ ስምንቱን የንግግር ክፍሎች ተረዳ)
በመጀመሪያ
- Nouns (ስም)
- Pronoun (ተውላጠ ስም)
- Adjective (ቅፅል)
- Verb (ግስ)
- Adverb (ተውሳካ ግስ)
- Preposition (መስተዋድድ)፣ እና
- Conjunction (መስተፃምር) የሚባሉትን በመማርና በመረዳት ጀምር።
የንግግር ክፍሎች ለመማር ቀላል ሲሆኑ በውስጣቸውም በተደጋጋሚ አገልግሎት ላይ የሚውሉ በርካታ ቃላትን ይዘዋል። የቃላቱን ትርጉም ብቻም ሳይሆን አገባባቸውንም ጭምር ያስተምራሉ።
ስለዚህ ተረጋግተህ እነዚህን ስምንት የንግግር ክፍሎች ተረዳ። ረጅም ጊዜ አይፈጁም።
እያንዳንዱን የንግግር ክፍል ስትማር ግን እየደጋገምክ ማንበብ፣ ማስታወሻ መያዝ፣ የራስህን አረፍተ ነገር እየመሰረትክ መለማመድና የመልመጃ ጥያቄዎችንም መስራት አትርሳ።
ስምንቱን የንግግር ክፍሎች እዚህ ጋ በአማርኛ ተፅፈው ታገኛቸዋለህ።
Step 2: Master Sentence Structure (የአረፍተ ነገር አወቃቀር ህግን ተማር!)
የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገር አመሰራረት ህግን ተማር። ስለ Subject, predicate, dependent clause, independent clause, ማጥናት አለብህ። ከዚያም እንድሁ ስለ simple sentence, ስለ compound sentence እና ስለ Complex sentence ማወቅ አለብህ። የዛኔ እንግሊዝኛህ በጣም እየዳበረ ይሄዳል።
Step 3: Study Verb Tenses (ቴንሶችን ተረዳ)
አንድ ነገር የተፈጸመበትን ወይም የሚፈጸምበትን ጊዜ የሚያመላክቱት ቴንሶች ናቸው። የእንግሊዝኛ ቴንሶች በሶስት ይከፈላሉ። እነሱም Past, Present እና Future ይባላሉ። እያንዳንዳቸው ደግሞ Simple, continuous, perfect, perfect continuous ተብለው በ 4 በ 4 ይከፈላሉ።
ሆኖም በብዛታቸው ተስፋ እንዳትቆርጥ፣ ለመማር በጣም ቀላል ናቸው። እንዳይረሱ ብቻ መደጋገም ነው የሚፈልጉት። ሁሉም የእንግሊዝኛ ግራመር ህጎች ቀላል ናቸው። እንዳይረሱ ብቻ ደጋግሞ ማንበብና መለማመድ ነው የሚጠይቁት። ቀላል ነገር ሁሉ አእምሮ ውስጥ ይቆያል ማለት አይደለም።
አንድ ነገር ምንም እንኳን ለመማር ቀላል ቢሆንም አንድ ጊዜ ብቻ ተምረነው አእምሯችን ውስጥ ቁጭ ብሎ አይቀርም፣ በተደጋጋሚ በማንበብ ውስጣችን ላይ ታትሞ እንዲቀመጥ ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚያ በኋላ ማንኛውንም ጽሁፍ አንብበን ለመረዳት፣ ሀሳባችንን በጽሁፍና በንግግር ለመግለፅ አንቸገርም፣ ምክንያቱም ህጉን እናውቀዋለን። ውስጣችን ላይ አለ።
ስለዚህ ስንፍናን ማስወገድና አንድን ትምህርት በጣም እየደጋገምን ማንበብ አለብን። ትምህርቱ ቀላል እንኳን ቢሆን አንድ ሁለቴ አንብበን በቃን ማለት የለብንም፣ በጣም ደጋግመን ማንበብ አለብን። በዚህ መልኩ ማንኛውንም ከባድና ብዙ ትምህርት መረዳትና ሸምድደን መያዝ እንችላለን።
የተማርከውን ህግ ወደ ተግባር መቀየር አትርሳ። ጊዜ ስታገኝ አረፍተ ነገር እየመሰረትክ ተለማመድ። ሌላ ስራ አትያዝ፣ ትርፍ ጊዜ ሲኖርህ ለሶሺያል ሚድያ ወይም ሰዎች ጋር ቁጭ ብሎ ለማውራት አታውለው፣ እንግሊዝኛህን ለማሳደግ ተጠቀምበት፣ መጽሀፍት አንብብ፣ የእንግሊዝኛ ንግግሮችን አድምጥ ወዘተ ብዙ መስራት ያሉብህ ነገሮች እያሉ ጊዜህን በከንቱ አታባክን።
Step 4: Learn Common Sentence Patterns (የእንግሊዝኛ ቃላት በአረፍተ ነገር ውስጥ የሚገቡበትን ቅደም ተከተል አጥና)
አሁን ለምሳሌ በአማርኛ አረፍተ ነገር ስንሰራ መጀመሪያ ላይ የምናስቀድመው ስምን ነው። መሃል ላይ የድርጊት ተቀባዩን መጨረሻ ላይ ግሱን ወይም ድርጊቱን ነው የምናስገባው። አሁን “አበበ በሶ በላ።” ብንል፣ መጀመሪያ ላይ ያለው ምንድን ነው? ስም ነው። አበበ የሰው መጠሪያ ስም ነው። ድርጊቱ የተፈፀመበት ደግሞ ያው ምስኪኑ በሶ ነው፣ በሶው ምን ሆነ? ተበላ። መጨረሻ ላይ የሚመጣው ድርጊቱ ነው። አበበ በሶውን ምን አደረገው? ለሚለው መልስ ይሆናል። ምን አደረገው? በላው። “አበበ በሶ በላ።”
ወደ እንግሊዝኛ ስንመጣ ደግሞ መጀመጀሪያ ላይ ያው የአረፍተ ነገር ባለቤቱን እናስገባለን፣ ቀጥለን መሀል ላይ ግን ግሱን እናስገባለን ate፣ ate ማለት ያው “በላ” ማለት ነው። መጨረሻ ላይ ድርጊቱ የሚያርፍበትን አካል እናስገባለን፣ ሰውም ይሁን ምግብም ይሁን የመልካምም ሆነ የመጥፎ ድርጊት ተቀባይ የሆነውን ድርጊት ተቀባይ ስም መጨረሻ ላይ እናስገባለን። ምሳሌ እንመልከት።
ፎርሙላው እንደዚህ ነው፦ S+V+O
Abebe ate food. አበበ ምግብ በላ። ልንል እንችላለን፣ ይህም SVO (subject-verb-object) ይባላል።
አንዳንዴ ደግሞ Abebe is a good boy. አበበ ጥሩ ልጅ ነው። ልንል እንችላለን፣ ይህም SVC (subject-verb-complement) ይባላል። a good boy የሚለው complement ወይም ማሟያ ይባላል።
አንዳንዴ “Abebe gave me a gift. አበበ ስጦታ ሰጠኝ።” እንላለን ይህም S+V+O+O ወይም (subject-verb-indirect object-direct object) ይባላል።
They named the baby Abebe. = ልጁን አበበ ብለው ስም አወጡለት። ይህም S+V+O+C (subject-verb- object-Complement) ይባላል።
ሌላም ብዙ የአረፍተ ነገር አይነቶች አሉ፣ እንደነዚህ አይነት የግራመር ህጎችን ማጥናቱ እንግሊዝኛ አንብበን የመረዳት ችሎታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳድገዋል።
ይሄንንም ፓተርን ወይም የቃላት አሰላለፍ በመጠቀም የራስህን አረፍተ ነገር በመስራት ተለማመድ። መጨረሻ ላይ በዚህ ነገር በጣም ጎበዝ ትሆናለህ።
Step 5: Identify and Correct Common Errors (በስህተት ጥቅም ላይ የዋሉ የእንግሊዘኛ ጽሁፎችንና ንግግሮችን እየለየህ አርም)
ከላይ ያሉትን ግራመሮች ከተማርክ በኋላ፣ የሰዎችን የግራመር ስህተት እየለየህ የማረም ልምድ አዳብር። የእንግሊዘኛ ተማሪዎች የሚሰሯቸውን የተለመዱ ስህተቶች እየለየህ ካጠናህ አንተም እነዛን ስህተቶች ደግመህ አትሰራቸውም፣ እንድሁም ስህተትን የመንገዘብ ችሎታህን ታሳድጋለህ።
ስህተቶችን ስታርም፣ በቀላሉ የ subject-verb agreement (መጣጣምን)፣ የ verb tense እና articles በትክክለኛው ቦታ ላይ መግባታቸውን ቸክ አድርግ።
Step 6: Practice Regularly (አዘውትረህ ተለማመድ)
ተስፋ ሳይቆርጡ በቋሚነት ልምምድ ማድረግ የእንግሊዝኛ ግራምመር ህግጋትን ለማወቅ ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
በየቀኑ ግራመር የምታነብበት፣ ጥያቄዎችን የምትሰራበት፣ የመፃፍ ልምምድ የምታደርግበት ሰአት መድብ።
በየቀኑ የእንግሊዝኛ ንግግሮችን አዳምጥ፣ ጽሁፎችን አንብብ፣ ለብቻህም ቢሆን የንግግር ልምምድ አድርግ፣ በእንግሊዝኛ መፃፍንም ተለማመድ።
Step 7: Seek Feedback and Guidance (የሰዎችን አስተያየትና ምክር ፈልግ)
ከእንግሊዝኛ አስተማሪዎች፣ ከጓደኞችህ፣ ወይም ማንኛውም ቋንቋውን ከሚችል ሰው ምክር ለማኘት አታመንታ። ግሩምና ገንቢ አስተያየቶችን ታገኛለህ። ስህተትህን ያርሙሃል፣ ችሎታህን የምታስተካክልበትን መንገድ ይጠቁሙሃል። በተለይ አስተማሪዎች የተቀመጡት አንተን ለመርዳት እስከሆነ ድረስ ጠይቃቸው። ይረዱሃል።
ማጠቃለያ፦
እንግሊዝኛህ በፍጥነት ይሻሻል ዘንድ እነዚህን አድርግ።
- ቅድሚያ ስምንቱን የንግግር ክፍሎች አጥና።
- ሁለተኛ የአረፍተ ነገር አወቃቀር ህግንና አላማቸውን ተማር!
- Study Verb Tenses (ቴንሶችን ተረዳ)
- Learn Common Sentence Patterns (የእንግሊዝኛ ቃላት በአረፍተ ነገር ውስጥ የሚገቡበትን ቅደም ተከተል አጥና)
- Identify and Correct Common Errors (በስህተት ጥቅም ላይ የዋሉ የእንግሊዘኛ ጽሁፎችንና ንግግሮችን እየለየህ አርም)
- Practice Regularly (አዘውትረህ ተለማመድ)
- Seek Feedback and Guidance (የሰዎችን አስተያየትና ምክር ፈልግ)
