ኮርስ 2፦ Parts of Speech (የንግግር ክፍሎች-የእንግሊዘኛ ግራመር ትምህርት)

በቀጥታ ወደ እንግሊዝኛ የንግግር ክፍሎች ከመሄዳችን በፊት፣ የእንግሊዝኛ ግራመርን የመማር ጥቅሙን ባጭሩ እንዳስሳለን።

ግራመር የመማር ጥቅሙ ምንድን ነው? 

  • ግራመር መማር፣ ጠቃሚና ሁልጊዜ አገልግሎት ላይ የሚውሉ በርካታ ቃላትን ለማወቅ ይጠቅማል።

    ግራመር መማር የንግግር እንግሊዝኛን በቀላሉ ለመሸምደድና ለማስታወስ ይረዳል። ግራመር ስንማር ያዳበርነው የማስታወስ ችሎታ ንግግሮችንም በትክክል እንዲናስታውስ ይረዳናል።

    አንድ ስፖርተኛ የጨዋታውን ህግ ሳያውቅ ወደሜዳ እንደማይገባው ሁሉ አንድ የእንግሊዘኛ ተማሪም የቋንቋውን ህግጋት ቢያቅ ከሰዎች ጋር ጥሩ ንግግር ለማድረግ ይረዳዋል። የጨዋታውን ህግ ስታውቅ ለመጫወት አትቸገርም።

    መሰረታዊ የግራመር ህጎችን አለማወቅ ማለት በጨለማ ውስጥ በግምት እንደመጓዝ ነው። 

በዚህ ኮርስ ስምንቱ የንግግር ክፍሎች ወይም The Eight Parts of Speech የሚባሉትን መሰረታዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ህግጋት በቀላል አቀራረብ ትማራላችሁ።

ሁሉም ትምህርቶች በአማርኛ ተዘርዝረው የቀረቡ ስለሆኑ ለመረዳት ቀላል ናቸው።

በእንግሊዘኛ ቋንቋ የግራመር ህግ ውስጥ ስምንቱ የንግግር ክፍሎች ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ። ትምህርቶቹም እንደሚታሰበው ከባድ አይደሉም፣ ቀላል ናቸው።

የቋንቋ እውቀታችንንም በከፍተኛ ሁኔታ ያሻሽላሉ።

እንዳይረሱ ብቻ ድግግሞሽ ነው የሚፈልጉት።

ቀላል ነገር ሁሉ አእምሮ ውስጥ ተቀምጦ ይቀራል ማለት አይደለም። ስለዚህ ስትማሩ መደጋገምና ማስታወሻ መያዝ አትርሱ።

  • እንግሊዝኛ የሚማር አንገብጋቢ ምክንያት ካለዎት ይሄን ኮርስ ይውሰዱ!
  • ይህ ኮርስ የጽሑፍና የንግግር ክህሎቱን ማሻሻል ለሚፈልግ ማንኛውም ተማሪ የተዘጋጄ ነው።
  • ከዚህ በታች፣ ሁሉም የንግግር ክፍሎች ተዘርዝረው ቀርበዋል።

This Post Has One Comment

Leave a Reply