ኮርስ 7፦ የእንግሊዝኛ መማሪያ ዘዴ

እንግሊዝኛንም ሆነ ማንኛውንም ቋንቋ ለመማር የሚረዳው የመጀመሪያው ምክር፣ “ሁሉንም ነገር በአንድ ጀንበር ለማወቅ አትሞክር። እንድሁም፣ በየቀኑ ሳታቋርጥ ትንሽ ትንሽ ነገር ተማር የሚለው ነው።”

እንግሊዘኛ መማር ጊዜ ይፈጃል፣ ስለዚህ ሁሉንም በአንድ ቀን ለማወቅ አትሞክሩ። ይልቅስ ሳታቋርጡ በየጊዜው የተወሰነ ነገር ለማወቅ ሞክሩ። እንድሁም ሁሉንም ጅምር ልቅቅ አታድርጉ፣ ከንግግር ከጀመራችሁ ንግግሩን እስከመጨረሻ ተማሩት። ግራመርም ከሆነ እንደዛው። የምትይዙትን የምትጨብጡትን ማጣት የለባችሁም። ተረጋጉና ተማሩ፣ ከዚያ ለውጥ ታመጣላችሁ! ለውጥን መጠበቅ ያለባችሁ ከተማራችሁ በኋላ ነው።

በዚህ ኮርስ የምትማሩት፦

  1. እንግሊዝኛን ለምን እንደምትማሩት ማወቅ እንዳለባችሁ፣ 
  2. እንግሊዝኛ ለመማር የሚረዳ ግብ እንዴት እንደምታወጡ፣
  3. የተማራችሁትንም እንደት እንደምትከልሱት፣
  4. የቃላት መሸምደጃ ዘዴዎችን 
  5. እንግሊዝኛ የመናገር ፍርሀትንም እንዴት እንደምትጋፈጡት ወዘተነው።

በአጠቃላይ በዚህ ኮርስ ስር እንግሊዘኛን በቀላሉ የምትማሩበትን መንገድ የሚያሳውቁና ቋንቋ ስለመማር ያላችሁንም የተሳሳተ ግንዛቤ የሚያርሙ ትምህርቶችን ታገኛላችሁ። እንግሊዘኛን በሚገባ ማወቅ ከፈለጋችሁ በዚህ ኮርስ ስር ያሉትን አጫጭር ትምህርቶች በትክክል ማንበብ አለባችሁ።

ከ Lesson 1: ጀምሩና እያንዳንዱን Lesson ስትጨርሱ Mark Complete የሚለውን እየነካችሁ ቀጥሉ። Mark Complete የሚለውን ስትነኩት በኋላ ምን ያህሉን ትምህርት እንደጨረሳችሁት ምልክት ይሆናችኋል።

Leave a Reply