Lesson 8: ከዚህ አንፃር እንግሊዝኛ በጣም ቀላል ነው

0

ከዚህ አንፃር ካየነው እንግሊዝኛ በጣም ቀላል ነው። 

ይህ የግራመር ህጉ የአማርኛን ያህል አይከብደም። ምክንያቱም ተመሳሳይ አረፍተ ነገሮችን ለተለያዩ ሰዎች፣ ለሴቱም ለወንዱም፣ ለተለያየ ጊዜም መጠቀም እንችላለን። ለምሳሌ ያህል ቀጥለው የቀረቡትን አረፍተ ነገሮች በአንክሮ እንመልከት፦

Example 1: Simple Present፦ 

Simple Present:

  • I walk to school every day. እኔ ሁልጊዜ ወደ ትምህርት ቤት እሄዳለሁ።
  • He walks to school every day. እሱ ሁልጊዜ ወደ ትምህርት ቤት ይሄዳል።

አሁን በእነዚህ የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮች ውስጥ ያሉት ነገሮች አብዛኞቹ ተመሳሳይ ናቸው። ሶስት ልዩነቶች ብቻ ናቸው ያሉት። እነሱም I, He, and S ናቸው። I እና He የሚሉትን ተውላጠ ስሞች ናቸው። walk የሚለው ግስ ላይም S የተጨመረበት ሶስተኛ ሰውን ለማመልከት ነው። He walks

የአማርኛው ግስ ላይ የጨመርነው ግን ብዙ ነው ይለያያልም።

በ Simple Past እና በ Simple Future አረፍተ ነገር ስንመሰርት መቀየር የሚኖርብን ተውላጠ ስሙን ብቻ ነው። በአማርኛ ግን ግሱንም እንቀይራለን። ለየተውላጠ ስሙ የሚጨመረው ግስም በጣም የተለያየ ነው። አሁንም ምሳሌውን እንመልከት፦

 ቀጥለን ደግሞ ዋና ግሱ ላይ ed ብቻ ነው የምንጨምረው። 

Simple Past፦

  • I walked to school yesterday. እኔ ትናንትና ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ።
  • He walked to school yesterday. እሱ ትናንትና ወደ ትምህርት ቤት ሄደ። 

(walk to walked for past tense)

Example 2: Using Different Pronouns in Simple Present

  • I read books every weekend. (እኔ በየሳምንቱ መጨረሻ መጽሀፍት አነባለሁ።)
  • She reads books every weekend. (እሷ በየሳምንቱ መጨረሻ መጽሀፍት ታነባለች።)
  • They read books every weekend. (እነሱ በየሳምንቱ መጨረሻ መጽሀፍት ያነባሉ።) 

Example 3: Future Tense አሁን ከተውላጠ ስሞቹ ውጭ ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው። 

  • I will finish the report tomorrow. = እኔ ነገ ዘገባውን እጨርሰዋለሁ።
  • We will finish the report tomorrow. = እኛ ነገ ዘገባውን እንጨርሰዋለን።
  • She will finish the report tomorrow. = እሷ ነገ ዘገባውን ትጨርሰዋለች።

Example 4: Present Continuous እዚህ ጋር የተወሰኑ ልዩነቶች ይኖራሉ። ሆኖም ግን አብዛኞቹ ተመሳሳይ ናቸው። 

  • I am cooking dinner right now. = አሁን ራት እየሰራሁ ነው።
  • She is cooking dinner right now. = እሷ አሁን እራት እየሰራች ነው።
  • They are cooking dinner right now. = እነሱ አሁን እራት እየሰሩ ነው።

Example 5: Modal Verbs (e.g., Can)

  • I can swim fast. እኔ በፍጥነት መዋኘት እችላለሁ።
  • He can swim fast. እሱ በፍጥነት መዋኘት ይችላል።
  • They can swim fast. እነሱ በፍጥነት መዋኘት ይችላሉ።

ይሄን ሁሉንም በኮርሱ ላይ ያገኙታል። የእንግሊዝኛን ከባድ ጎኖች እዚህ ያንብቡ። 

Leave a Reply