Back to: ኮርስ 2፦ Parts of Speech (የንግግር ክፍሎች-የእንግሊዘኛ ግራመር ትምህርት)
4. Article (አመልካች ቅጽል)
Article/ አመልካች ቅጽሎች ስለየትኛው ነገር ወይም ሰው እያወራን እንደሆነ ይጠቁማሉ። በእንግሊዝኛ ቋንቋ ውስጥ ከስም እና ከቅጽል በፊት እየገቡ የሚያመለክቱ ሦሥት ዓይነት Articles ወይም አመልካች ቅጽሎች አሉ፤እነሱም፦ a፣ an እና the ናቸው።
Articles (አመልካች ቅጽሎች) Indefinite articles (ያልተወሰኑ አመልካቾች) እና Definite article (የተወሰነ አመልካች) በመባል በሁለት ይከፈላሉ። Indefinite articles (ያልተወሰኑ አመልካቾች) የሚባሉት “A እና An” ሲሆኑ፤ Definite article (የተወሰነ አመልካች) የሚባለው ደግሞ “The” ነው።
Indefinite articles (ያልተወሰኑ አመልካቾች) የሚባሉት “A” እና “An” ከነጠላ ስሞች እና ከሚቆጠሩ እንዲሁም በቅጡ ተለይተው ከማይታወቁ ስሞች በፊት ይገባሉ።
Definite article (የተወሰነ አመልካች) የሚባለው “The” ደግሞ ከነጠላ እና ብዙ ስሞች፤ ከሚቆጠሩ እና ከማይቆጠሩ ስሞች እንዲሁም ተለይተው ከሚታወቁ ስሞች በፊት ይገባል። ቀጥለን እያንዳንዳቸውን በዝርዝር እንመለከታለን
ስለ አመልካች ቅፅሎች የሰራሁት ቪዲዮ አለ። ትምህርቱ የበለጠ እንዲገባችሁ እዚህ ጋ እሱን መመልከት ትችላላችሁ።
The indefinite article (ያልተወሰነ አመልካች) “A”
“A” ከነጠላ ስሞች፣ ቅጽሎች፣ ከሚቆጠሩ ግን በቅጡ ተለይተው ከማይታወቁ ስሞች በፊት ይገባል፤ እንዲሁም “A” መነሻቸው Consonant Sound (የተነባቢ ፊደል ድምፅ) ካላቸው ስሞች እና ቅጽሎች በፊት ይገባል። ምሣሌ፦
- Do you wear a uniform to school? ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ መለያ ትለብሳለህ?
- Can you hear a bird singing? የምትዘምረዋ ወፍ ትሰማሃለች?
- Mom bought me a new dress today. እናቴ ዛሬ አዲስ ቀሚስ ገዛችልኝ።
- An elephant and a mouse fell in love. አንድ ዝሆንና አንዲት አይጠ መጎጥ በፍቅር ወደቁ።
በተጨማሪም የማንኛውም ቃል የመጀመሪያ አናባቢ ፊደል እንዴ “Y/የ” የሚነበብ ከሆነ ቃሉን ያልተወሰነ አመልካች ቅጽል “A” ይቀድመዋል። ምሣሌ፦
- A European country. አንዲት አውሮፓዊት ሀገር
- A university professor. አንድ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር
- A useful thing. አንድ ጠቃሚ ነገር
- A unique object. አንድ ልዩ ነገር
- A one-time event. የአንድ ጊዜ ክስተት
- A one-eyed monster. አንድ ዓይና ጭራቅ
Indefinite article (ያልተወሰነ አመልካች) “An”
“An” ከነጠላ ስሞች ወይም ቅጽሎች፣ ከሚቆጠሩና በቅጡ ተለይተው ከማይታወቁ ስሞች ወይም ቅጽሎች በፊት ይገባል። ይሄ ያልተወሰነ አመልካች ብዙውን ጊዜ ከአናባቢ ፊደሎች (A, E, I, O, U) እና በአናባቢ ድምፅ ከሚጀምሩ ቃላት በፊት ይገባል። ለምሣሌ፦
- My wife was recently in an automobile accident. ባለቤቴ በቅርቡ የመኪና አደጋ ደርሶባት ነበር።
- Do you work in an office? ቢሮ ውስጥ ነው የምትሰራው?
- An elephant and a mouse fell in love. አንድ ዝሆን እና አንዲት አይጠ መጎጥ በፍቅር ወደቁ።
- An idiot man laughed at me. አንድ ደደብ ሰውዬ በኔ ላይ ሳቀብኝ።
- An ugly incident has happened. አንድ አስቀያሚ ክስተት ተፈጥሯል።
- She has an idea. እሷ አንድ ሀሳብ አላት።
- She bought an umbrella. እሷ አንድ ዣንጥላ ገዛች።
- I ate an apple and an orange. እኔ አንድ ፖም እና ብርቱካን በላሁ።
- They have an excuse for everything. እነሱ ለሁም ነገር ሰበብ አላቸው።
እንዲሁም ፊደል“H” ተውጦ ቀጥሎ ያለው አናባቢ ፊደል በሚነበብበት ጊዜ ከቃሉ በፊት “An” ይገባል። ለምሣሌ፦
- It will take me an hour to do that. ይህን ለመስራት አንድ ሰዓት ይወስድብኛል።
- I will not take more than an hour. ከአንድ ሰዓት በላይ አልፈጅም/አልቆይም።
- She is an honorable woman. እሷ የተከበረች ሴት ናት።
- Meeting the president was an honor for me. ፕረዜዳንቱን ማግኘት ለእኔ ክብር ነበር።
- An honest person becomes always happy and peaceful. ሐቀኛ ሰው ሁል ጊዜ ደስተኛ እና ሰላማዊ ይሆናል።
The definite article (የተወሰነ አመልካች) “The”
“The” ነጠላ እና ብዙ ስሞችን ለመጠቆም ያገለግላል። ይሄ አመልካች ቅጽል በውሉ ተለይተው ለሚታወቁ ስሞች ብቻ ያገለግላል። ለምሣሌ፦
- Please close the door. እባክህ በሩን ዝጋው።
- Turn the TV off now. አሁን ቲቪውን አጥፋው።
- I will wait for you in the car. መኪናው ውስጥ እጠብቅሃለሁ።
- I saw the elephant at the zoo. እኔ ዝሆኑን በመካነ አራዊቱ ውስጥ አየሁት።
በቀላሉ ነጠላ እና አጠቃላይ ወይም ላልተወሰኑ ነገሮች “A” እና “An” እንጠቀማለን፤ ነገር ግን ስለ አንድ የተወሰነ ነገር በምናወራበት ጊዜ “the” ን እንጠቀማለን። ለምሣሌ፦
- “A cat” (ድመት) ካልን በዓለም ላይ ያለ ማንኛውንም ያልተወሰነ ድመት ማለታችን ነው፤ ነገር ግን
- “The cat” (ድመቷ) ካልን በአጠገባችን ያለችን ድመት ወይም አንዲት ተለይታ የምትታወቅን ድመት እየጠቆምን ነው። ለምሣሌ አንድ አስተማሪ
- “Let us read the ” “መጽሐፉን እናንብብ።” ቢል እናንብብ እያለ ያለው አንድን የተለየ መጽሐፍ ወይም በእጁ የያዘውን መጽሐፍ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን
- “Let us read a ” “መጽሐፍ እናንብብ።” ካለ ግንዛቤያችንን ለማዳበር ማንኛውንም በውል ተለይቶ ያልታወቀን መጽሐፍ እናንብብ ማለቱ ነው።
በቀጣዩ ትምህርት እንደዚሁ በጣም ወሳኝ የሆኑ አራት ትምህርቶችን እንማራለን። ይሄን ወይም ከዚህ ስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ያንብቡት።
